ለመኸር እርሻ ከ82 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የቡርጂ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
የቡርጂ ዞን ግብርና መምሪያ የአዝርዕት ሰብሎች ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ቦጋለ ጅራ 2017/2018 መኸር እርሻ 83 ሺህ 5 መቶ 55 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን አቅደው ከዚህም ውስጥ 82 ሺህ 3 መቶ 63 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች መሸፈናቸውን አንስተው ከተዘሩ ሰብሎችም 70 በመቶ ቦሎቄ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተዘራው ሰብል ከ1 ሚሊዬን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት ቡድን መሪው አንስተዋል።
የነፍሳት ተባይ፣ የበሽታ ተባይና አረም ምርትን የሚጎዱ ስለሆኑ አርሶ አደሩ አረሙን በወቅቱ በማንሳት ተባይ ከተከሰተም ለግብርና ባለሙያዎች በማሳወቅ ሁል ጊዜ ማሳቸውን ከትትል እንዲያደርጉ አቶ ቦጋለ አሳስበዋል።
የወረዳው ጉዴ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተመስገን ፀቤ በበኩላቸው፤ የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብና ግንዛቤ በማስጨበጥ ለአርሶ አደሮች ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ካነጋገርናቸው አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር አደን ጋሮ፣ ኦዳ ጡኮ እና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት አሁን ማሳ ላይ ያለው ሰብል ጥሩ ደረጃ በመሆኑ የአርም ቁጥጥር ስራ ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ቦጋለ ሉሳ – ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን

More Stories
በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ተጠቅሞ በመስራት ከህገወጥ ስደትና ከድህነት መላቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ
በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ፣ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል መፍጠር ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
የኮሌጁንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ የማስተሳሰር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ