ኤስ ኦ ኤስ ኢትዮጵያ የሀዋሳ የህፃናት መንደር በሆሳዕና ከተማ ለሚገኙ ሶስት ትምህርት ቤቶች 11 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየሰራ ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ሀዋሳ ቅርንጫፍ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ገልጿል።
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኤስ ኦ ኤስ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ህፃናት መንደር ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ደጀኔ፤ ለትምህርት ቤቶች የሚደረግ ድጋፍ ትውልድን በማሰብ የሚደረግ ሲሆን ድርጅቱ ከሚሰራባቸው የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ ትምህረት ነው ብለዋል።
ለትምህርት ጥራት መሻሻል የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በዕለቱ የተደረጉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ በማድረግ በኩል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ አሳስበዋል።
ፕሮጀክቱ በዕለቱ በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለሶስት ትምህርት ቤቶች 11 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው የትምህር ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን በኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር አራዳ ፕሮጀክት ተወካይ ወ/ሮ ቅድስት ወንድዬ ገልፀዋል።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አድነው ባፋ፤ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚሰራው ስራ ኤስ ኦ ኤስ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እያደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ድጋፍ የተደረጉ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ከመጠቀም አንፃር የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ፕሮጀክቱ ያደረገው ድጋፍ ለታለመለት ዓለማ መዋል እንደለበት አሳስበዋል።
ኤስ ኦ ኤስ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በሆሳዕና ከተማ አሰተዳደር ድጋፍ ባደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱኔ ገልፀዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በበኩላቸው፤ ድርጅቱ በትምህርት ቤቶች እያደረገው ባለው ድጋፍ በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ታይቷል ብለዋል።
በተለይም በተማሪዎች በኩል ይስተዋሉ የነበሩ መጠነ ማርፈድና መድገም ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን አመላክተዋል።
ቀጣይም በዕለቱ የተደረጉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በአግባቡ በመጠቀም የተሻላ ውጤት ለመምጣት እንደሚረዳቸው በማንሳት ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዘጋቢ: አሚና ጀማል – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የተለያዩ የህክምና መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት መቻላቸውን በሚዛን አማን ከተማ በማህበረሰብ አቀፍ ፋርማሲ ሲገለገሉ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገለፁ
የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በሣጃ ከተማ እየተከበረ ነው
በክረምት ወራት የታየውን ትጋት በበጋውም ለመድገም ቁርጠኞች መሆናቸውን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ