በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ባለፈው ዓመት የተከናወኑ ተግባራት በርካታ ችግሮችን የፈቱ አንደነበሩ ተገለፀ

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ባለፈው ዓመት የተከናወኑ ተግባራት በርካታ ችግሮችን የፈቱ አንደነበሩ ተገለፀ

‎በወረዳው የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

‎መድረኩን ያስጀመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔ፤ በእያንዳንዱ አገልግሎት መስክ በንቃት በመሳተፍ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን አካላት አመስግነው፤ የተጀመሩ በጎ ተግባራትን ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

‎የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አየለ፤ ወጣቶችን 18 በሚሆኑ ዘርፎች በማሳተፍ ችግር ፈቺ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።

‎በአረንጓዴ አሻራ የግብርና ሥራዎች ከ23 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ ከታቀደው በላይ ማከናወን መቻሉን ጠቅሰው፤ 5 መቶ 18 የሚሆኑ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች ግንባታና ጥገና መደረጉን ገልጸዋል።

‎55 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፈበት በክረምቱ መርሀግብር 136 ሺህ የሚሆኑ ወገኖችን ተጠቃሚ በማድረግ አገልግሎቱ በገንዘብ ሲሰላ 58 ሚሊዮን ብር እንደሚሆንም ገልጸዋል።

‎በአገልግሎቱ ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል ወጣት መክብብ ደሳለኝና ኃይሉ ተሰማ፤ ማንም ሳያስገድዳቸው በራሳቸው ፈቃድ በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ገልጸው በዋጋ የማይተመን እርካታ ማግኘታቸውን አስረድተዋል።

‎ዘጋቢ፡ አማኑኤል ትዕግሥቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን