ታራሚዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ በስነ ምግባርና በሙያ ታንፀው በቴክኖሎጂ ሽግግር ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 20/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ታራሚዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ በስነ ምግባርና በሙያ ታንፀው በቴክኖሎጂ ሽግግር ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ።
የህግ ታራሚዎችም በተቋሙ በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ፤ ታራሚዎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ እነሱም የሌሎችን መብት አክብረው በስነ ምግባርና በሙያ ታንፀው በቴክኖሎጂ ሽግግር ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የህግ ታራሚዎች በተደራጁበት የስራ መስክ የሚያመርቱትን ምርት ለማህበረሰቡ በማቅረብ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ ከጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጋር በመነጋገር የመሸጫ ቦታ ለማመቻቸት እየተሰራ እንዳለም አስረድተዋል።
በተቋሙ የማረምና ማነፅ ተሀድሶ ልማት ዲቪዥን አስተባባሪ ኮማንደር ደመቀ እንዳለ፤ በ2018 ዓ.ም ታራሚዎች በማሽነሪ፣ በጋርመንት፣ በእደ ጥበብ፣ በሽመናና በሌሎች የሙያ መስኮች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግና በማህበር በማደራጀት የመስሪያ ቦታ ተመቻችቶላቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የህግ ታራሚዎች በሰጡት አስተያየት በማረሚያ ቆይታቸው የባህሪ ለውጥ አምጥተው በተቋሙ በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን የእርምት ጊዜያቸውን አጠናቀው ከማህበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ በሰለጡኑበት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት ሰላማዊና አምራች ሀይል እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ብልጽግናን ለማረጋገጥ የፖሊስ አመራር እና አባላትን አቅም ማሳደግ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ህዳር 29 ለሚከበረው የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የአሰልጣኞች ሥልጠናና ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ በካራት ከተማ እየተካሄ ይገኛል
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ባህል፣ ማንነትን ቅርስን ከማስተዋወቅ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ገለፁ