የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
ተጠርጣሪዎችም የከተማው ፖሊስ ላበረከተው አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
የመስቀል በአል በአደባባይ ከሚከበሩ አበይት በዓላት መካከል ቀዳሚው መሆኑ ይታወቃል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጥሩነሽ ተስፋዬ በማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩ ተገኝተው ለተጠርጣሪዎች ባስተላለፉት መልእክት፤ የመስቀል በዓል የተጣላ የሚታረቅበትና በአብሮነት የሚከበር በአል በመሆኑ የከተማው ፖሊስ ላሳየው ፍቅርና አክብሮት አመስግነዋል።
በጋሞ ብሔረሰብ ዘንድ ለእንስሳትም ለሰው የጥጋብ ወቅት ተብሎ የመስቀል በአል እንደሚታመን አብራርተው፤ ለተጠርጣሪዎች ማዕድ በማጋራት አብሮነታቸውን ያሳዩ የፖሊስ አባላትን ልምድ በመቅሰም በሌሎችም ተቋማት ሊለመድ ይገባል ብለዋል።
የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገበየሁ ፃራ፤ የወጣቱን ስብዕና በመገንባት ሰላም ወዳድ እንዲሆን በማነፅ ረገድ የከተማው ፖሊስ ጠንካራ ስራ መስራቱን ገልፀው በጣቢያው የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የወንጀል አስከፊነትን በመረዳትና ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፖሊስ ጎን በመቆም የልማት ተሳታፊ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ወንጀል ማህበራዊ ክስተት በመሆኑ በየትኛው አጋጣሚ ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ወገኖች እኛ በምንሰጠው ፍቅር ደስተኛ እንዲሆኑና ወንጀልን የሚፀየፉና ሰላም ወዳድ እንዲሆኑ በማሰብ የመስቀል በዓልን ከተጠርጣሪዎች ጋር ማዕድ በማጋራት በጋራ ማሳለፋቸውን አስታውቀዋል።
በፖሊስ ጣቢያው የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በተደረገላቸው አብሮነት መደሰታቸውን ገልፀው፤ ከጣቢያው ወጥተው ህብረተሰቡን ሲቀላቀሉ ፖሊስንና ህብረተሰቡን ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የሳሮ እና ዳሮስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ስራ አስኪያጆች ከከተማው ፖሊስ ጋር በአብሮነት ለተጠርጣሪዎች ማዕድ በማጋራታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የተለያዩ የህክምና መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት መቻላቸውን በሚዛን አማን ከተማ በማህበረሰብ አቀፍ ፋርማሲ ሲገለገሉ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገለፁ
የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በሣጃ ከተማ እየተከበረ ነው
በክረምት ወራት የታየውን ትጋት በበጋውም ለመድገም ቁርጠኞች መሆናቸውን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ