የመስቀል በአል ከሀይማኖታዊ ስርአቱ ባሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ

በአርባምንጭ ከተማ የመስቀል ደመራ በአል በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።

‎የመስቀል ደመራ በአል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ ከሚከበሩ በአላት መካከል አንዱ ሲሆን በአብሮነትና በጋራ የሚከበር ታላቅ በአል መሆኑን የአርባ ምንጭ ከተማ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ተናግረዋል፡፡

‎ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበችው የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ከሃማኖታዊ ስርአቱ ባሻገር ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክርና ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ምዕመናኑ ገልፀዋል።

‎ይህንን ባህላዊና ሀይማኖታዊ ይዘት ያለውን ታላቅ በአል ሳይበረዝ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አስታውቀዋል።

‎በአርባምንጭ ከተማ የደመራ በአል ሀይማኖታዊ ስርአቱን ጠብቆ በድምቀት አየተከበረ ይገኛል።

ዘጋቢ፡- ገነት መኮንን