የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የመስቀልን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!
እንኳን ለብረሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!፤ አደረሰን! እያልኩ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
ባለብዙ ቀለም፣ መስኩ ለምለም፣ ዜጎች ለአዳዲስ ሰኬቶች የሚነሳሱበት የተስፋና የብርሃን ወቅት በሆነዉ ወርሃ መስከረም የሚከበረው የመስቀል በዓል ልዩ ድምቀት ያለዉና በሃይማኖታዊና ማህራዊ እሴቶችና ትሩፋቶች የታጀበ ነዉ።
ተፈጥሮ ምድርን ደማቅና ዉብ አድርጎ በሚያሸበርቅበት፣ የአዲስ ዓመት ማግስት የሚከበረዉ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ አስተምህሮዉና ማህበራዊ ትዉፊቶቹ ለአዳዲስ ሰኬቶች የሚያነሳሱ ናቸዉ።
በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ከሃይማኖታዊ እሴቶቹ ባሻገር ማህበራዊ ትሩፋቶቹ በርካታ ናቸዉ።
ተራርቀዉ የሠነበቱ ቤተሰቦች፣ ተገናኝተዉ ቤተሰባዊ ፍቅራቸዉን የሚወጡበት፣ ሐሴታቸዉን የሚገልፁበት ነዉ።
የተስፋ ብርሃን፣ የፅናት፣ የአሸናፊነትና የመስዋዕትነት ምልክት የሆነዉ የመስቀል በዓል የአብሮነት፣ የተስፋና የትጋት እሴቶችን እንድናጠናክር የሚያግዝ ነዉ።
በዓሉ የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት፣ ለሠላምና ለልማት ግንባታ በአጠቃላይ ለሁለንተናዊ ብልጽግና በጋራ ለመትጋት የምንነሳሰበት እንዲሆን እመኛለሁ።
መልካም የመስቀል በዓል!
አመሠግናለሁ !

More Stories
በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ተጠቅሞ በመስራት ከህገወጥ ስደትና ከድህነት መላቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ
ለኢኮኖሚ እድገት የሚያግዙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መነቃቃት እያሳዩ መሆናቸው ተገለጸ
በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ፣ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል መፍጠር ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ