የባስኬቶ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ሥራ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ ከትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 15/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ)የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪ ቀረቧል።
በመድረኩም በዋናነት የተማሪ ውጤት ወድቀት በጥልቀት የተገመገመ ሲሆን የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በቅንጅትና በዕቅድ ሊሰራ እንደሚገባ ተመልክቷል።
የባስኬቶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ማርቆስ ልፋቱ ለትውልድ ተቆርቋሪ በመሆንና ያለንን እውቀት በማጋራት የትምርህት ሥራዓት ፍሰትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ያሳሰቡት የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬው ፍሻለው አሰራርን በመፈተሽ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የዞኑ አስተዳደር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የትምህርት ሥርዓትን ለመበደል የሚጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ኢ/ር ፍሬው ለሙያቸው ክብር ለማይሰጡና አሰራርን በሚጥሱ አካላት ላይ አሰራርን በተከተለ መንገድ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢንጂነር ዘማች ካንሶ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረጽ የአሰራር ግድፈቶችን በማረምና ግብ በመንደፍ የትምህርት አመራሩና ባለሙያዎች በመነጋገርና በመረዳዳት በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ቅንጅታዊ አሰራርን በማስፈን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ሀይሉ ገልጸዋል።
የመምህራን የዝግጅት ማነስ፣ ልማዳዊ አሰራርን መከተል፣ የትምህርት አመራር ከትምህርት ባለሙያ ጋር ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣ ተተክሎ አለመስራት፣ ድጋፍና ክትትል ማነስ፣ ይዘትን አለማጠናቀቅና የትምህርት ክፍለ ጊዜ ብክነት ለዉጤት ማነስ ዋነኛ መንስኤዎች መሆናቸውን በመድረኩ በስፋት ተዳሷል።
ዘጋቢ ፡-ዓቢይ ይኼይስ

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
የወረዳውን ዕድገት ለማፋጠን የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ተቋማት ሊፋጠኑ ይገባል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በወ/ሮ አዱኛ አዛዥ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ