የጋዜጠኞችን አቅም በማጎልበት የመፈጸም አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጋዜጠኞችን አቅም በማጎልበት በዜና፣ ፕሮግራም እና በአርትኦት ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
የአርባምንጭ ኤፍኤም 90.9 ከተመሠረተበት ሰኔ 2001 ዓ.ም ጀምሮ በ 9 የብሔረሰብ ቋንቋዎች የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና ለህብረተሰቡ በመድረስ ሁሉን አቀፍ ለውጥ እንዲመዘገብ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ም/ስራ አስኪያጅና ይዘት ስራዎች ዘርፍ አስተባባሪ አቶ በኃይሉ ሙሉጌታ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ለተከታታይ 3 ቀናት በዜና እና ፕሮግራም አዘገጃጀት እንዲሁም በአርትኦት ሥነ-ምግባር ዙሪያ የሚሰጠውን ስልጠና ጋዜጠኞች በንቃት ተከታትለው የተሻለ ዕውቀት እንዲጨብጡ አሳስበዋል።
የደሬቴድ አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ጉጃ ጉሜ በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የመፈጸም አቅም ለመገንባት ተቋሙ የያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ የሚሰጥ ስልጠና በመሆኑ አርታኢያንና አዘጋጆች ከስልጠናው ጉድለታቸውን የሚሞሉበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልፀዋል ።
የማስፈጸም አቅም ማሻሻል የሚቻለው በልምድ እና ዕውቀት የበቁ ባለሞያዎችን መፍጠር ሲቻል መሆኑን አብራርተዋል።
በሬዲዮ ዜና ፣ ፕሮግራም እንዲሁም ከቴሌቪዥን ዜና እና ፕሮግራም አዘገጃጀት እና አርትኦት እንዲሁም ሥነ-ምግባር አንፃር የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማረም የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም አዋጭ መንገድ ነው ብለዋል።
ተቋሙ የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ በሚሰጠው ስልጠናን ሰልጣኙ በአጽንኦት እንዲከታተል አቶ ጉጃ አሳስበዋል።
ዘጋቢ ፡ አሰግድ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ