የጎፋ ጋዜ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ በዓል በጋራ መከበሩ አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ጋዜ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ በዓል መከበሩ አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የበዓሉ ተሳታፊዎች ገለጹ።
በዓሉ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት በመሸጋገራቸው አምላካቸውን የሚያመሰግኑበት፣ ለሀገራቸው እና ለሕዝባቸው ሠላምና ጠንነትን፣ ጥጋብ እና ደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ የሚያከብሩት በዓል ነው።
በበዓሉ ላይ የተገኙ የዞኑ ተወላጆች በሰጡት አስተያዬት በዓሉ ከአሮጌ ወደ አዲስ ዓመት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገር ምልክት መሆኑን ገልጸው፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት ነው ብለዋል።
የዘንድሮው በዓል በዶ/ር ዮናታን ጀረነ እና በዶ/ር ቦሻ ቦንበ የተዘጋጀው የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች ባህልና ታሪክ መጽሐፍ በተመረቀበት ወቅት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ከአጎራባች ዞኖች የተገኙ ተጋባዥ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያዬት በዓሉ አንድነትንና አብሮነትን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
ተጋባዥ እንግዶች ለጎፋና ኦይዳ ህዝቦች አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የአብሮነት፣ የመቻቻልና የመከባበር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ