የጠምባሮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “መሳላ” በዓል በሙዱላ ከተማ እየተከበረ ነዉ
ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጠምባሮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “መሳላ” በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በሙዱላ ከተማ በአደባባይ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሀዲ፡ የክልልና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
አመራሮቹ የፎቶ አዉደ ርዕይንና የጠምባሮ ብሔረሰብ ባህላዊ ምግቦችንም ጎብኝተዋል፡፡
ከአጎራባች መዋቅሮች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶችም ለልዩ ወረዳዉ የሰንጋ ስጦታ በርክተዋል፡፡
የጠምባሮ መሳላ በዓል የጠምባሮ ብሔረሰብ አዲስ ዓመቱን የሚቀበልበት በዓል ነዉ።
ዘጋቢ፡ ድልነሳው ታደሰ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ