የኣሪ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ መምሪያ የፐብሊክ ሰረቫንት ቀንን በማስመልከት በአፈፃፀማቸው የተሻሉ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጣቸው

የኣሪ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ መምሪያ የፐብሊክ ሰረቫንት ቀንን በማስመልከት በአፈፃፀማቸው የተሻሉ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጣቸው

ሠራተኞችን መመዘን፣ ማበረታታትና መደገፍ ብሎም ማሰልጠን በሚሠሩባቸው ዘርፎች በተሻለ ሞራል ሥራቸውን እንዲከውኑ ያስችላል፤ ይህ ደግሞ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ጭምር ነው ያሉት የኣሪ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አሸብር ጋልሶ ናቸው።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንደገለፁት፤ ፐብሊክ ሰርቫንት በሀገሪቱ ለውጥ ሂደት ውስጥ አይተኬ ሚና አላቸው።

በበቂ ሁኔታ ሠራተኞችና ሀብት በሌለበት በውስን ባለሙያዎች በጋራ ቅንጅት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት የሠሩ አካላትን አበረታትው፤ በቀጣይም ጠንክረው እንዲሠሩ አሳስበዋል።

ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች ለዞኑ ለውጥና ውጤት አንዱ ከሌላው ልምድ በመቅሰም በትጋት እንዲሠሩ ዋና አስተዳዳሪው መልዕክት አስተላልፈው፤ የዕውቅና አሰጣጡ በተቻለ መጠን በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።

ዕውቅና የተሰጣቸው ፈፃሚዎችና የተቋም አመራሮች መመሪያን በተከተለ መልኩ ተግባራትን በቁርጠኝነት በመፈፀም ለውጤት መብቃታቸውን ገልፀው፤ በተሰጣቸው ዕውቅና ተደስተው በቀጣይም ይበልጥ ተግተው እንደሚሠሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመርሐ ግብሩ የጡረታ ጊዜያቸው ደርሶ የሚወጡ አካላትም ዕውቅና ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን