የጉራጌ ዞን የጸጥታ ምክር የ2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

የጉራጌ ዞን የጸጥታ ምክር የ2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

ሀዋሳ፡ መስከረም 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጉራጌ ዞን የጸጥታ ምክር ቤት ”ሰላማችን በማጽናት ለልማታችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንተጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ የ2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ የህያ ሱልጣን ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዞኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎችን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበርና ለማስቀጠል ሰላም መሰረታዊ ግብኣት በመሆኑ ሰላምን መጠበቅ ያስፈልጋል።

ሰላም እና ጸጥታ ያለህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት አቶ የህያ በተለይም በከተሞች የህዝብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱን አመላክተዋል።

የዞኑ መሰረታዊ የጸጥታ ችግሮች በመለየትና እንዲፈቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመምራት አበረታች ውጤት መመዝገቡና በዞኑ አንጻራዊ ሰላም በማስፈን የልማት ተሞክሮ መቀመሪያ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የጸጥታ ተቋማት ዋነኛ ተልዕኮ የሆነውን የዜጎች ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ እንዲሁም ሀገርና ህዝብን ከየትኛውም ጥቃት የመከላከል እና ግቦችን ለማሳካት የጸጥታ ምክር ቤቱ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ተከትሎ መስራት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣ የዞኑ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ከዞን ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ መላኩ ንማኒ – ከወልቂጤ ጣቢያችን