ነዋሪዎቹ የቅርሱ መመለስ አሁን ያለዉ ትዉልድ የቀደሙ አባቶችን ታሪክ እንዲያውቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ብለዋል።
ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ መንበረ መንገሻ፣ ትዝታ ጸጋዬ፣ አቶ ተቋመ ታደሰ እና ምክትል ኢንስፔክተር ዳዊት ዳሄሮ፤ ለበርካታ አመታት ከአካባቢው ተወስዶ የቆየው የንግስና ዘውድ እና መቀመጫ በአግባቡ ተጠብቆ በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ይህንን ታሪካዊ እለት በአደባባይ ወጥቶ መዘከር ዳግም ውልደት ነዉ ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ይህ ሁነት ልጆቻችን ታሪካቸውን በአግባቡ እንዲያውቁና እንዲኮሩበት የሚያደርግ ይሆናል ብልዋል።
የዘንድሮዉ የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ የሆነዉ ማሽቃሬ ባሮ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆና ጥንታዊው የካፋ ነገስታት የንግስና ዘውድ እና መቀመጫ ወደ ስፍራዉ ተመልሶ የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብልዋል።
ታሪክ ከሚዘከርባቸዉ ጉዳዮች አንዱ የቀደመዉ ትዉልድ የሚገለገልባቸዉ ቁሶች በቅርስ መልክ ተቀምጠዉ ለትውልድ እንዲተላለፉ መሆኑ ነዉ ያሉት ነዋሪዎቹ፤ አሁን ላይ ያለዉ ትዉልድ የራሱን ታሪክ በተመቻቸለት አጋጣሚ ሊጎበኘዉ ይገባል ብለዋል።
ትውልዱ የራሱን ታሪክ አዉቆ ሌላ ታሪክ እንዲሰራ ታስቦ ለተደረገዉ እንቅስቃሴም የዞኑን አስተዳደር አመስግንዋል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
በጋራ ተባብረን የህዳሴ ግድብን እንዳሳካን የማህበረሰባችን የጤና ችግሮችን በተለይም እናቶችንና ህጻናትን በዘላቂነት ከወባ በሽታ መታደግ እንችላለን – ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር)
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስኬት ለወደባችን ጉዞ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነው ሲሉ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ
የካፈቾ ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተከበረ