በኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የሥራ ጉብኝት አደረጉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማህበራዊ ክላስተር በጂንካ ከተማ የሚገኙ የክልል ጤና ቢሮ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ኦክሲጂን ማዕከልና በክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጂንካ ህብረተሰብ ላቦራቶሪ ማዕከል ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ነብዩ ቤዛ የጉብኝቱን አላማ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ደረጄ ዱጎማ (ዶ/ር) በክልሉ በላፉት ጊዜያት በከፈተኛ ሁኔታ ተከስቶ የነበረውን የወባ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወባ ክትባት ዘመቻ ያስጀምራሉ ብለዋል።

በጤና ተቋማት ለዜጎች የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ለማቀላጠፍ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን ጉብኝቱ በየአካባቢው ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠልና ውስንነቶችን በማረም በኩል ከፈተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖር ተመልክቷል ።

ዘጋቢ፡ ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን