“በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ አሁን ላይ አንፃራዊ ሠላም በመገኘቱ የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ ልማት መግባት ችሏል” ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ
በዞኑ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።
አቶ ዳዊት አሰፋና አቶ ባዬ አወቀ በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ነዋሪዎች ናቸው።
ነዋሪዎቹ በወረዳው ባለፉት አመታት ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በአካባቢው ልማትና ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል
አሁን ላይ በወረዳው አንፃራዊ ሠላም በመገኘቱ የአካባቢው ማህበረሰብ ወደ ልማት መግባት መቻሉን ነው የተናገሩት።
በወረዳው የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
የጉራፈርዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ ከርካ ከዚህ ቀደም በወረዳው በነበረው የፀጥታ ችግር ለበርካቶች ሞት መፈናቀል የንብረት ውድመት ምክንያት ሆኖ እንደነበር ጠቁመዋል።
የወረዳውን ሰላምና ልማት ዳግም ለመመለስ አመራሩ በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ አካላትና የሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመቀናጀት ሰፊ ስራ መስራቱን ነው የተናገሩት፡፡
በአሁኑ ወቅት ወረዳው ወደ ቀደመ ሰላሙ በመመለሱ ያሉ አልሚ ባለሀብቶችን ጨምሮ ማህበረሰቡ ወደ ልማት ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኮጁ ባዳካች በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት አመታት በተለያዩ ወረዳዎች የተለያዩ አጀንዳዎችን መነሻ በማድረግ ፀረ ሠላም ሀይሎች የሠላም ዕጦት እንዲፈጠር ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን በ2017 ዓ.ም በመኸር እርሻ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን አቅዶ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ