የአገር አቀፍ የህጸናት ፓርላማ የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራትና የመደበኛ እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ
በዚሁ መድረክ የ2016 ዓ.ም የህጸናት ፓርላማ መነሻ እቅድ ዙሪያም ውይይት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ህጸናት ፓርላማ ዋና አፈ ጉባኤ ህጻን ቅዱስ ሞላ በዚሁ ጊዜ እንዳለው ፓርላማው የህጻናትን መብትና ደህንነት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ ዘርፉን ከሚደግፉ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል።
የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሙድ በበኩላቸው የህጸናት የመማር መብታቸው እንዲረጋገጥ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እንዲሁም ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል።
የሁሉም ክልል የህጸናት ፓርላማ አፈ ጉባኤዎች የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም እና በሂደቱ የተገኙ ተሞክሮዎችንና ያጋጠሙ ችግሮችን ሪፖርት በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የፓርላማ አባለቱ በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራሞች በመሳተፍ ችግኞችን መትከል፣ ለተቸገሩ ህጸናት የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ ድጋፎችን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ማድረግ መቻላቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
“ተወደደሪና ንቁ ሕጻናት ለዘመናዊት ኢትዮጵያ”፣ “ለዛሬዎቹ ሕጻናት ፍቅርና በጎነት እናውርስ” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአፍሪካ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ በነገው ዕለት ይከበራል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን በ2017 ዓ.ም በመኸር እርሻ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን አቅዶ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ