ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ጳጉሜን 5 – የነገው ቀን “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ ተከብሯል።
በዓሉን ልዩ የሚያደርገው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቅ ማግስት መከበሩ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፤ የነገው ቀን በዋናነት ዲጂታል ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፤ ሀገራችን ይኽንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እያጠናቀቀች ነው ብለዋል።
ጳጉሜ የሀገራችን መለያ ብቻ ሳትሆን፤ የአባቶቻችን የቀን አቆጣጠር ቀመር የበላይነትን የምታሳይ መሆኗን ገልጸዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
2017 ዓመተ-ምህረት የጋራ ትርክት የተፈጠረበትና በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎች የተመዘገቡበት ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።
ብዝሃ-ኢኮኖሚ የተፈጠረበትና በኮሪደር ልማቱ የተረሱ ከተሞች የተነቃቁበት መሆኑን አስረድተዋል።
ያለፈው ዓመት ማህበራዊ ዘርፍን በማሻሻል የአገልግሎት ተደራሽነት ዘመናዊ የተደረገበት ነው ብለዋል።
የአንድ መሶብ አገልግሎት በሀገር ደረጃ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠትን ያሳየ መሆኑን ገልጸው፤ በቅርቡ ወደ ክልልና ዞን እንደሚወርድ ተናግረዋል።
ለዚህም ኢትዮ-ኮደርስ አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አስራት አዳሮ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
ለተነሱ ሃሳብ አስተያየቶችም ምለሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ የክልሉ፣ የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-