የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
ጊዜን፣ ፀጋዎችን፣ የመልማት አቅሞችን፣ ሌሎችንም ዕድሎች ከወትሮው በተለየ መንገድ፣ በተስፋና በፅናት መንፈስ፣ በይቻላል የእመርታ መነፅር ማስተዋል፤ ለእመርታዊ ለዉጥ ብርቱ ዐቅም ይሆናል።
ለእመርታዊ ለዉጥ፣ እመርታዊ እይታ፣ እመርታዊ ሀሳብ ያሻል። የሀሳብ እመርታ፣ የጉዳዮች መመልከቻ መነፅር ከፍ እንዲል፣ የእይታ እጥፋት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ለፈጠራና ፍጥነት ምክንያት ይሆናል፤ የትጋትና የዉጤት እመርታ እዉን እንዲሆንም ያስችላል።
የማይቻሉ የሚመስሉ ጉዳዮች እንደሚቻሉ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በእመርታዊ እይታና ትጋት ያሳካናቸዉ ጉዳዮች ምስክሮች ናቸዉ። እናም እያንዳንዱን ቀን፣ እያንዳንዱን ወር በአጠቃላይ ጊዜን፣ እዉቀትን፣ ጉልበትን፣ ፀጋዎችን፣ የሕዝብ ዐቅሞችን፣ የመልማት እምቅ ዕድሎችን…ወዘተ በእመርታ መነፅር መግራት፣ መምራት ለእመርታዊ ለዉጥ መሠረት ነዉ።

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ