የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገር በቀል እሳቤዎች ሀገራዊ አቅሞችን መጠቀም ያስቻሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና በርካታ የልማት ኢኒሼቲቮችን በመተግበር እንዲሁም የተረጂነትና የጠባቂነት አስተሳሰብንና አመለካከትን በመስበር፤ አይቻልም በተባሉ መስኮች ጭምር ምርታማነትን በማሳደግ የታሪክ ዕጥፋት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዕውን በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት የጣሉ አስደናቂ እምርታዎችን ማስመዝገብ ችለናል፡፡
በሁሉም የኢኮኖሚ እድገት ዘርፎች እና የዘላቂ ልማት ግቦች ማሳካት የቻልነው ተጨባጭ እምርታዊ ለውጥ፤ የጠራ ራዕይ በመሰነቅ፤ ተቋማዊ አቅሞችን በማጎልበትና በየወቅቱ የሚገጥሙንን ፈተናዎች ተባብረን በጽናት በመሻገር በእጃችን ያሉን ፀጋዎችና የመልማት አቅሞች በአግባቡ ተጠቅመን በህብረት ተግተን በመስራት ባጭር ጊዜ ውስጥ ብልጽግናችንን በተሟላ ሁኔታ በእጃችን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ናቸው።
ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን በጋራ ጥረትና ትጋት እናረጋግጣለን!!
“እምርታ ለዘላቂ ልማት ከፍታ”

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ