ዘላቂ ሠላምን በማፅናት የሐገርን እድገት ለማረጋገጥ ከምንግዜውም በላይ ተባብሮ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ
በባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳና በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ መካከል የዕርቀ ሠላም ኮንፍረንስ ተካሂዷል።
በባስኬቶ ዞንና በደቡብ ኦሞ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የቡናባሳ ቀበሊያትና ሰላማጎ ወረዳ በመእኒት ጶዲ ብሔረሰብ መካከል ለረዥም ጊዚ የሠላም መደፍረስ ሲያገጥም እንደነበረ የተመላከተ ሲሆን፥ በሰው ህይወትና በልማት ሥራዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያስከትን እንደነበረ ጠተቁሟል፡፡
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ የየዞኑ አመራሮችና ነዋሪዎች ለሠላም ባላቸው ጽኑ አቋም መነሻ በተደረገው ሰፊ ውይይትና ጥረት የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም ግርማ ገልጸዋል።
የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢ/ር ፍሬው ፍሻለው “ፅኑ መሠረት ብርቱ ሐገር” በሚል እንደ ሐገር ታስቦ በዋለው ጳጉሜ 1 ቀንን አስመልክቶ በሁለቱ ዞኖች መካከል ዘላቂ ዕርቀ ሠላም ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል።
ያለፈውን ቂም፣ ቁርሾና የዕኩይ አላማ አስፈጻሚ አካላትን ተግባር ወደ ጎን በመተው በሁለቱ ዞኖች መካከል የነበረውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኋላፊ አቶ ታደለ ጋያ በሁለቱም ዞኖች ያለውን የመልማት ዕምቅ አቅም ተጠቅሞ በጋራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማምጣት ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ብቸኛው አማራጭ ነው ብለዋል።
በዕርቀ ሠላም መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በቀለ ኮርማ የክልሉን መረጋጋትና ሠላም የማይፈልጉ ጥቂት ግለሰቦች በሁለቱ ዞኖች መካከል ሰፊ ግጭት፣ ዝርፊያና ግድያ እንዲፈጸም ሲሰሩ መቆዬታቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስትም ይህንን ተረድቶ ለሠላም ባለው ፅኑ አቋም መነሻ በየደረጃው ሰፊ ውይይት በማድረግ ለዛሬው መግባባት መደረሱን አረጋግጠዋል።
የባስኬቶና የደቡብ ኦሞ ዞኖች የመጣውን ሠላም በማፅናት፣ ዘላቂ እድገትን በማረጋገጥ የህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።
የባስኬቶ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አለም አጎናፍር ዕርቀ ሠላም ስምምቱን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሐይማኖት አባቶች፣የሐገር ሽማግሌዎችና ባለድርሻ አካላት የእርቅ ሥነ ሥረዐቱን የፈጸሙ ሲሆን ዞኖቹ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሐሣብ በማዕከላዊ ኢትዮያውያ ክልል ሣጃ ክላስተር እየተከበረ ነው
የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ስራው ተጠናቆ ለምረቃ መድረሱ እንዳስደሰታቸው በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
በቀሪ ጊዜ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ወደትምህርት ገበታ በማምጣት ወላጆች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ