በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ

በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለፁ።

የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት የ2017 በጀት አመት አፈፃፀምና የ2018 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ እና የፍርድ ቤቶች ጥምረት በፍትህ ዘርፍ ላይ ዘርፈብዙ ለውጥ ለማምጣት አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

በተገልጋይ እርካታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ከፍርድ ቤቶች ያላቸው ጥምረት ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ እና ባልተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነትን በሚያሳድጉ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረግ እንደሚገባም ነው ያስረዱት።

በመድረኩ ላይ የጥምረቱ ዋና ሰብሳቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬን ጨምሮ የዞንና ልዩ ወረዳ አፈጉባኤዎች እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ ፍስሀ ክፍሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን