የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል ሲከበር የእርሳቸውን አርዓያ በመከተል መልካም ተግባራትን በማከናወን ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቦንጋ ከተማ አስተዳደር የተንጎላ መስጂድ አስተዳዳሪ አሚር መሐመድ ከድር ለ1500ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ህዝበ-ሙስሊሙ የነብዩ መሐመድን የልደት በዓል ሲያከብር የእርሳቸውን ደግነት፣ ሰው አክባሪነትና መልካም አርአያነት በመከተል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ነብዩ መሐመድ ለተራበ የሚመግቡ፣ የተቸገረን ሁሉ ጠያቂና የመልካም ስብዕና ባለቤት በመሆናቸው ፤ የእርሳቸውን በጎ ባህርይ መላበስ ይገባል በማለት አሳስበዋል።
የነብዩ መወለድ ህዝበ-ሙስሊሙ ብርሀን እንዲመለከት ያስቻለ በመሆኑ፤ ይህንን ብርሀን በመከተል ለአላህ ተገዢ መሆን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በሁሉም አካባቢዎች በዓሉ ሲከበር ለኢትዮጵያ ሠላም ዱአ በማድረግና ለተቸገሩ ወገኖች በመድረስ እንዲሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም እንኳን ለ1500ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት ቀን በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ታምሩ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የክልሉን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በመቅረፍ የውሀ ሽፋኑን ለማሳደግ ከተለያዩ ተራድኦ ድርጅቶች ጋር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የተሻሻለ የላም ዝሪያ በመጠቀም የወተት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የጊምቦ ወረዳ አስተዳደር ገለጸ
የነብዩ ሙሐመድ የመውሊድ በዓል ሲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ፈለጋቸውን ተከትሎ በእለቱ ከተዘጋጀው ለአቅመ ደካሞች በማካፈል ማክበር እንደሚገባ የይርጋጨፌ ኑር መሰጅድ እማም ሼክ ከድር አደም አስታወቁ