ማህበረሰቡ ግብርን በወቅቱ በመክፈል ከተለያዩ አስተዳደራዊና ህጋዊ ቅጣቶች ራሱን እንዲጠብቅ ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን ቆጶ፤ ገቢ የአንድ አካባቢ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ መሰረት መሆኑን በመገንዘብ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በወረዳው በተጀመረው የ2017/18 ገቢ ግብር አሰባሰብ ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ከ5 ሚሊዮን 476 ሺህ ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ብለዋል።
ለገቢው ከፍተኛ መሆንም ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የተጨመረው 38 በመቶ የግብር ምጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ እንደተወጣ ተናግረዋል።
በወረዳው 1 ሺህ 68 የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች እንደሚገኙ የተናገሩት ኃላፊው፤ ከእነዚህም 161ዱ እስካሁን ግብር አልከፈሉም ብለዋል።
101 ደረጃ “ሀ” እና 34 ደረጃ “ለ” ነጋዴዎች ግብራቸውን በማሳወቅ እየከፈሉ ስለመሆናቸው አንስተዋል።
በተለይም የደረጃ “ሀ” እና “ለ” አንዳንድ ነጋዴዎች የተሳሳተና ሀሰተኛ የሂሳብ መዝገብ በማቅረብ የመንግስትን ገቢ እንዳያጭበረብሩ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በወረዳው በበጀት ዓመቱ ከማዘጋጃና መደበኛ ከ343 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከአሁን ከ18 ሚሊዮን 800 ሺህ ብር በላይ ማሳካት እንደተቻለ ገልጸዋል።
የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰብ ገቢ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው፤ የደረጃ ለውጥና የደረሰኝ አጠቃቀም ስራዎችን ለአብነት አንስተዋል።
እስከአሁን 81 ነጋዴዎች የደረጃ ሽግግር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ካነጋገርናቸው ግብር ከፋዮች መካከል አቶ አዱኛ አይናቸው፣ መ/ር አማን አባገሮና አባድር ዳውድ፤ ግብር በወቅቱ መክፈል ለአካባቢው ዕደገት ጉልህ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
ሁሉም አካላት ሰርቶ ከሚያገኘው ገቢ ግብር መክፈልን ባህል ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ አሰግድ ሣህሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
ህብረት ስራ ማህበራት በተደራጁበት ዓላማ ለአባሎቻቸው የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በጠንካራ አደረጃጀትና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ሊደገፉ እንደሚገባ ተመላከተ
የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችና መምህራንን በመደገፍ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ
የክልሉን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚችል የፖሊስ መዋቅር መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ