በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ
የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ደምሴ እንደገለፁት ከወቅቱ ቴክኖሎጂ ጋር የሚራመድ በዕቅድ የሚመራና የመፈፀም አቅሙን በየጊዜው የሚያሳድግ፣ የተገልጋይ እርካታን የሚፈጥር ባለሙያና ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም ቆጥሮ የሚፈፅም ባለሙያ ከመፍጠር አንፃር ተግዳሮቶች እና ውስንነቶች በመኖራቸው የሰቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ከዕቅድ ጀምሮ ባሉ የለወጥ ሥራዎች ዙርያ በወረዳው ላሉ ሲቪል ሰርቫንት በሃና ከተማ ሰልጠና ሰጥቷል።
ከዕቅድ ጀምሮ በአገልጋይነት መንፈስ የሚሰራውን ሥራ በአግባቡ አውቆት መፈፀም እንድችል ስልጠናው ማሰፈለጉን አመላክተዋል።
የህዝብ ክንፍን ያሳተፈ የምዘና ሥርዓት ሊጠናከር እንደሚገባም ተመላክቷዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)