በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ሰብሎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አስታወቁ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ሰብሎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አስታወቀዋል፡፡

በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን የጉራፋርዳ ወረዳ አርሶ-አደሮች በበኩላቸው ፤ በሩዝ ምርት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በ2017 በልግ አዝመራ ከ359 ሺህ ሔክታር በላይ ማሳን በማልማት ከ14 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደስራ መገባቱን ገልጸው በዚህም 394 ሺህ ሄክታር ማሳ በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

እስካሁን ከ180 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የነበረ የሰብል ምርት መሰብሰቡን ጠቁመው ከተሰበሰበው ምርትም ከ6.5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ በበልግ አዝመራ ከለሙ ሰብሎች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው በቆሎ ሲሆን ፤ 261 ሺህ ሄክታር በላይ የማሳ ሽፋን ያለው ነው።

ከበቆሎ ሰብል ብቻ ከ11.6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝ ነው አቶ ማስረሻ የተናገሩት።

ከዚህ ቀደም የሩዝ ሰብል ልማት በአካባቢው ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመው ፤ አሁን ላይ በበልግ አዝመራ በተሰራ ስራ ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ለማግኘት ታቅዶ የምርት አሰባሰብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።

ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ስንዴን እና ሩዝን የመሳሰሉ ሰብሎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የተሰሩ ስራዎች ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።

አቶ እሸቱ ታደሰ እና ተስፋዬ እሸቴ በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ አርሶ-አደሮች ሲሆኑ ፤ በበልግ አዝመራ ያለሙትን የሩዝ ምርት ሲሰበስቡ እና ሲወቁ በማሳቸው ተገኝተን አነጋግረናቸዋል፡፡

በአካባቢው ያልተለመደውን የሩዝ ምርት በግብርና ባለሙያዎች ምክረ-ሀሳብ በመታገዝ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በቤተሰብ ደረጃ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ለገበያ የሚሆን በቂ ምርት እያገኙ መሆናቸውን የተናገሩት አርሶ አደሮቹ ፤ ከአንድ ሄክታር የሩዝ ማሳ ከ35 እስከ 40 ኩንታል እንደሚያገኙ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ- ዮሐንስ ክፍሌ ከቦንጋ ጣቢያችን