ኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዲጅታል ክህሎትን በማስጨበጥ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዲጅታል ክህሎትን በማስጨበጥ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዲጅታል ክህሎትን በማስጨበጥ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።

በቴክኖሎጂ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለመና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ኢንሼቲቭ መሆኑን ሰልጣኝ ወጣቶች ተናግረዋል።

ኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭን ያለምንም ወጪ ስልካቸውን በመጠቀም የዲጅታል ክህሎታቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚናገረው ወጣት ኤፍሬም ኤርሚያስ እና አትጠገብ መሠረት፤ ለሎች ወጣቶችም ስልጠናውን በመውሰድ በቴክኖሎጂ ራሳቸውን እንዲያበለፅጉ አስገንዝበዋል።

የዳሰነችና የማሌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ከተማ እና ምንቶብ ሉፖ እንዳስረዱት፥ በጠቅላይ ሚንስተሩ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ወጣቶች ስልጠና ውጤታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

ኢንሼቲቡ የዲጅታል ክህሎትና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑን የገለፁት የደቡብ ኦሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ት ብሩክታዊት አኮ፥ በ2018 ዓ.ም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የኢንተርኔት ችግርን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሠሩም አስረድተዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የዞኑ ኢትዮ – ኮደርስ ስትሪንግ ኮሚቴ ሰቢሳቢ አቶ ታደለ ጋያ በበኩላቸው፥ ቴክኖሎጂውን ያወቀ ወጣትና መንግስት ሠራተኛ በመፍጠር ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ አለም ገበያ እንዲቀላቀሉ የሚያስችል ኢንሼቲቭ በመሆኑ ለዘርፉ የዞኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን