በመኸር እርሻ ከ4ሺ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን አቅዶ እየሰራ መሆኑን የቁጫ አልፋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለጸ
አርሶአደር መስፍን ማንደፎ በወረዳው ኮዶ ዎኖ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፤ በ 2 ሄክታር ማሳ ላይ በማህበር ተደራጅተው ሰብል በማምረት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር በበቂ መጠን እና ጊዜ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።
ሌላኛው አርሶአደር ሳባ ሳና ዝናብን ጠብቀው የመኸር እርሻ ስራ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው መሬታቸውን በዘመናዊ የእርሻ ትራክተር በማረስ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ቢፈልጉም አቅርቦት ባለመኖሩ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡
የቁጫ አልፋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን በርገኔ እንዳብራሩት በ2017/18 መኸር በልዩ ትኩረት ከሚሰሩ የግብርና ተግባራት መካከል ጤፍ እና ቦለቄ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ ተናግረዋል ።
በአጠቃላይ 4ሺ 2 መቶ 46 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ የማሳ ሽፋኑ 89 ከመቶ ደርሷል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በዘር ከተሸፈነው ማሳ 317 ሺህ 7 መቶ 80 ኩንታል ምርት ለማምረት ግብ መጣሉን አውስተው ከዚህ ውስጥ በዋና ዋና ሰብል በአጠቃላይ 2ሺህ 9 መቶ 62 ሄክታር ይለማል ብለዋል።
ዘጋቢ ፦ አሰግድ ተረፈ ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በስብዕና ግንባታ ስራ ላይ በማተኮር በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ገለፀ
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለአረጋዉያን ያስገነባዉን የመኖሪያ እና እንክብካቤ ማዕከል ስራ አስጀመረ
የትምህርት ዘርፍ መጠናከር ሀገሪቱ ወደ አዲስ የስልጣኔ ማማ ለመድረስ ለምታደርገው ጉዞ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ