በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ኮይቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 3 ልጆችን ተገላገለች
ከዚህ በፊት አራት ልጆችን በአራት ዙር የወለደች ሲሆን በአምስተኛው እርግዝና ሦስት ልጆችን መውለዷን ሆስፒታሉ አስታውቋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ የካሌንዶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ገናሜ፤ በቅድመ ክትትል ሂደት ሦስት ልጆችን ማርገዟ ታወቆ ክትትል እየተደረገ መቆየቱን የኮይቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም አምባቸው አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
አምባቸው አሰፋ (ዶ/ር) አክለውም በሆስፒታሉ ከሁለት በላይ መንትያ ሲወለድ የመጀመሪያ መሆኑን ገለጸው ከተወለዱ ሕፃናት ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ አንዷ ሴት መሆኗንና ሦስቱም ህጻናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
በአንድ ጊዜ ሶስት ልጆችን በሰላም በመገላገሏ ደስተኛ መሆኗን የገለጸችው ወ/ሮ አዳነች ገናሜ፤ በሆስፒታሉ ከክትትል ጀምሮ እስከወሊድ ቀን ድረስ የጤና ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርባለች።
ዘጋቢ: ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)