ተቋማት በተደራጀ እቅድ እንዲመሩ ጥሪ ቀረበ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ተቋማት በተደራጀ እቅድ እንዲመሩ የካፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ አሳሰበ።
መምሪያው የ2017 ዓ.ም አፈጻጸሙን እና የአዲሱን በጀት ዓመት እቅዱን በቦንጋ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
የካፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ገብሬ መምሪያው በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት መርህ ተግባራትን በአግባቡ እየገመገመና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር የተገናዘበ እንዲሆን እየሰራ ነው ብለዋል።
ተቋማት እቅዶችን ሲያዘጋጁ የተቀመጡ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ሊሆን ይገባል ያሉት አቶ ሀብታሙ ፤ በአግባቡ መፈተሽ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የማህበረሰቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ሊፈቱ በሚችሉና በጥራት በተዘጋጁ እቅዶች መመራት ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን በቀለ በተደራጀ እቅድ መመራት ተግባራትን ከግብ ለማድረስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
አቅምን ያገናዘቡ እቅዶች የማህበረሰቡን መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ አስተዋጽኦ እንዳላቸው መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የፕላንና ልማት ሴክተሮች በየአካባቢው ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መከታተልና ያሉበትን ደረጃ መገምገም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በመድረኩ የ2017 አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ እየተገመገመ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
”ሠላምን ማፅናት ለክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ መካሔድ ጀመረ
በሀዲያ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ
የክረምት ዝናብን ተከትሎ ጎርፍ እና መሰል አደጋዎች በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ