የ2018 የኢትዮጵያ የግብርና ናሙና ጥናት መረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የ2018 የኢትዮጵያ የግብርና ናሙና ጥናት መረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና በአርባ ምንጭ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ስታስትስቲክስ ኤጀንሲ የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስሜ አንበሴ እንዳሉት ከግብርና ጋር የተያያዙ ወጥነት ያላቸው አዳዲስ መረጃዎችን ለማሰባሰብ እና ለፖሊሲ አውጪዎች ግብአት ለማቅረብ ጥናቱ ያግዛል።
አክለውም የመረጃ ሠራተኞች ስልጠናውን በትጋት በመከታተል ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብ አገራዊ ሐላፊነታቸውን እንዲወጡ ሀላፊው መክረዋል።
የግብርና ነክ ናሙና ለጥናቱ በግብርናው ምርም ብሎም ለቀጣይ ፖሊሲ አውጪዎች ያለው ሚና የጎላ ነው ያሉት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ደግፈ አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው።
በግብርና ናሙና ጥናት ስልጠና ላይ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 8 ዞኖች የተወጣጡ ከ290 በላይ ስልጣኞች በመሳተፍ ላይ ያሉ ሲሆን በእርሻ በቤት፣ እንስሳት፣ በንብ እና ሌሎች ግብርና ነክ መረጃዎች ላይ ያተኮረ ነው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ወረዳው በስፋት እየለማ ያለውን የስንዴ ምርጥ ዘር ለክልሉ ዞኖች ማከፋፈል መጀመሩን አስታወቀ
ህዝበ ሙስሊሙ ከአካባቢ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንድነትና ሠላም እንዲረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ የኣሪ ዞን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለፀ
የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው