ህፃናትን ከጉልበት ብዝበዛ ለማዳን በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ተጠየቀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 06/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህፃናትን ከጉልበት ብዝበዛ ለማዳን በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡
ዓለም አቀፍ የህፃናት ጉልባት ብዝበዛ ማስወገድ ቀን በአዲስአበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
በህጸናት ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በድራማ መልክ ያሳየውንና ችግሩን በጋራ ለመፍታት በሚያግዙ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የሚደረግበትን መድረክ ያዘጋጀው ደግሞ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ከኖርዌይ ሠራተኛ ማህበር ኮንፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ነው።
“ህጻናት” ማለት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በባህሪው የልጆችን ልጅነት የሚነጥቅ ፣ ክብር የሚያሳጣ፣ አካላዊና ሥነ አዕምሯዊ እድገታቸውን የሚጎዳ እንዲሁም የትምህርት ዕድላቸውን የሚያጣብብ እና የሚዘጋ እንቅስቃሴ ነው።
ህጻናትን በባርነት ወይም ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ አስገድዶ ማሰራት ፤ ህጻናትን መሸጥና በህገ ወጥ መንገድ ማዘዋወር ፤ህጻናትን ለውትድርና በመመልመልና በመቅጠር ለግጭትና ለጦርነት ማሰራት እንዲሁም ህጻናትን ለወሲብና ወሲብ ቀስቃሽ በሆኑ ትዕይንቶች ማሰማራት አስከፊ ከሆኑ የህጸናት ጉልበት ብዝበዛዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አያሌው አህመድ እንደገለጹት በዓለማችን 160 ሚሊዮን ህፃናት፣ በአፍሪካ 72 ሚሊየን ህፃናት በኢትዮጵያ ደግሞ እድሜያቸው ከ5 እስከ 17 ውስጥ የሚገኙ 51 በመቶ የሚያህሉ ህጻናት ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)