በመከላከያ ሠራዊት የማዕከላዊ ዳሎል እዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ሐማኒ ቀበሌ አስጀመሩ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአንድ ጀምበር 21 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ የተከላ መርሐ-ግብሩ ተጀምሯል።
በዛሬው እለት በካፋ ዞን ከ5.4 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።
በተከላ መርሐ-ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጊምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ፤ በጊምቦ ወረዳ ከ530 ሺህ በላይ ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል።
የካፋ ዞን ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት መምሪያ ኃላፊ ጋዎ አባመጫ፤ ማህበረሰቡ ደንን ጠብቆ በማቆየቱ የተፈጥሮ ሚዛን ተጠብቆ መቆየቱን ተናግረዋል።
ደን ተጠብቆ በመቆየቱ አካባቢው ለዓለም አስፈላጊ አካባቢ መሆኑ ተመስክሮለታል ነው ያሉት።
በወረዳው ባለፉት ስድስት ዓመታት 215 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውንና የፅድቀት ደረጃቸው 92 በመቶ መሆኑን እንዲሁም ከተተከሉ ችግኞች ውጤት ማግኘት መቻሉን አስታውቀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በበኩላቸው፤ በለውጡ መንግስት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ስራ ሰባተኛ ዓመቱን ማስቆጠሩን አስታውሰው የሚተከሉ ችግኞች ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።
ሀገርን የመገንባት ስራዎች አንዱ አካል ነው ያሉት አቶ አንድነት፤ ከመትከል ባለፈ መንከባከብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊን ጨምሮ የጊምቦ ወረዳና የካፋ ዞን አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ ክፍሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ
“በክልሉ ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች ለኢኮኖሚ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ ሆነዋል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ