በነገው እለት እንደ ሀገር ለሚተከለው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 1.6 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መዘጋጀታቸውን የምእራብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መልኬ ኬላጌ ተናገሩ
በዞኑ ችግኞችን ወደተከላ ስፍራ ከማጓጓዝ ባለፈም 1.7 ሚሊየን ጉድጓዶች መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል።
የምእራብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መልኬ ኬላጌ እንደተናገሩት በሰባት ወረዳ እና በሶስት የከተማ አስተዳደሮች በበልግ እና በመኸር ወራት 18 ሚሊየን የተለያዩ አይነት ችግኞች በበጀት አመቱ ተዘጋጅተው እስካሁንም 12 ሚሊየን ያህል ችግኞች ተተክለዋል።
በነገው እለት በአንድ ጀንበር ለሚከናወነው የተከላ ፕሮግራምም 1.6 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመው፤ ለዚሁ ተግባርም 1.7 ሚሊየን ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
1.2 ሚሊየን ሀገር በቀል የሆኑ የፍራፍሬ፣ የመኖ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የውጪ ሀገር ዝርያ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውንም አቶ መልኬ ጠቁመዋል።
ለተከላው በዞኑ 43 ሳይቶች መመረጣቸውን የጠቆሙት አቶ መልኬ፤ ከተመረጡት ሳይቶች ውስጥ አስሩ ቀጥታ ወደ ሲስተም የሚገቡ እና 42.6 ሄክታር የሚሸፍኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
በተከላው ከአስሩ መዋቅር የተውጣጡ ከ150 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አቶ መልኬ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2018 በጀት ዓመት ከ2 ቢሊዮን 62 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ
ለሕዝቡ የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ
የCRFL ፕሮጀክት ያለፉት አምስት ዓመታት አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ነው