በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ

በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአባላት ኮንፍራንስ ተካሂዷል።

በሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ህብረት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአበላት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ፥ ባለፉት ዓመታት በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን ተናገረዋል።

በፓርቲው ጠንካራ አመራርና አበላትን በመፍጠር ብልሹ አሰራርና የተሳሳተ አመለካከትን በማረም ከተሰራ ሀገራችንን ለማልማት ምቹ መሆኑን የቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።

በክልሉ የመጣው አንፃራዊ ሰላም በአበላቱና በአመራሩ የመጣ ለውጥ መሆኑን የገለፁት አቶ ፋጂዮ፥ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዘበዋል።

የሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ጸደቀ ከፍታው በበኩላቸው፥ በአባላት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ላይ እንደተናገሩት በሚዛን አማን ማዕከል የሚገኙ የክልል ቢሮ የተጠሪ ተቋማት አባላት በቤተሰብ ደረጃ እንዲሁም እንደ ህብረት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከመሪዎች ጋር በመፈራረም ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።

በመድረኩም አባላትን ከማፍራትና ጠንካራ የፓርቲ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠርና በማጠናከር ረገድ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ቢሆንም አባላት በበቂ ሁኔታ የማፍራትና ቤተሰብ በማድረግ ረገድ ተጠናክሮ ሊሰራ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምዴ ፋሪስ የህብረቱን የ2018 ዕቅድ አቅርበው የመድረኩ ተሳታፊዎችም በአፈጻጸም ሪፖርትና ዕቅዱ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በማጠቃለያ ኮንፈረስ ላይ ከተሳተፉት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት መካከል አቶ ሳምሶን ባድንስ፣ ቤቴልሄም ዳንኤልና አቶ ጌትነት መንገሻ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል በሁሉም ዘርፍ በፓርቲና በመንግስት ህብረተሰቡን በማስተባበር የተከናወኑ ተግባራት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

አስተያየት ሰጪዎች አውስተው በሰላም፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በፖለቲካዊ ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል የአባላቱ ግንባር ቀደም ሚና ወሳኝ ነው መሆኑን አብራርተዋል።

በተለይም አበላቱ ዕቅዶችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ፣ የውስጠ ፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከርና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማጎልበት እንዲሁም አዳዲስ አባላትን ማፍራትና በሁሉም ተቋም ፓርቲን በመትከል ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎች ገልፀዋል።

በመጨረሸም በሚዛን አማን ማዕከል የሚገኙ የክልል ተቋማት፣ የቢሮና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና የሚዛን አማን ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አባላት የሚዛን አማን ኤርፖርት የግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ በመጎበኘት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአባላት ኮንፍራንስ ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን