“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

በመረሃ ግብሩ የተገኙ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደገለፁት በየዓመቱ የተተከሉ ችግኞች ለውጥ እያሳየ መምጣቱን ተናገረዋል።

በተለይ ባለፉት 5 እና 6 ዓመታት የተተከሉ ችግኞች እንደሀገር በርካታ ውጤቶችን አስመዘገበዋል ያሉት ኃላፊው፥ የ2017 የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር በክልሉ በቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ መካሄዱን ገልፀዋል።

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር እንደክልል በዳሮ ዞን እንደሚከናወን አቶ ፋጂዩ ጠቁመው፥ የተተከሉ ችግኞችን በተገቢው ዝግጅት በማደረግ መንከባከብ ከአባላቱ እንደሚጠብቅ ኃላፊው አብራርተዋል።

የሚዛን አማን ማዕከል የክልል ተቋማት ብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ፀደቀ ከፍታውና አቶ ከበደ ተስፋዬ የህብረቱ ምክትል ሰብሳቢ በሰጡት አስተያየት የክላስተሩ ብልፅግና ፓርቲ አመራርና አበላት “በመትከል ማንሰራራት“ በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር በጋራ ማካሄዳቸውን ተናገረዋል።

የችግኝ ተከላው የተሻለ ሀገርና ተፈጥሮን ለትውልድ ለማሻገር በጠቅላይ ሚኒስተሩ የተጀመሩ የአረንጓዴ አሻራ በሚከናወነው ተግባር የራሳቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናገረዋል።

በሚዛን አማን ከተማ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የተተከለው አረንጓዴ አሻራ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ማንጎና አቫካዶ እንደሚገኙበትም ገልፀዋል።

የ2017 ክልላዊ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ከ21 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን