በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮላንጎ ከተማ እያካሄደ ነው

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮላንጎ ከተማ እያካሄደ ነው

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኧሌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ውድነሽ ሽቱ እንደገለፁት፤ ምክር ቤቱ በሕገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት የሕዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሲሠራ መቆየቱን አስረድተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በ7ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀትና በብቃት በመወያየት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።

ምክር ቤቱ ጉባኤውን ያለፈውን ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ የጀመረ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት ዞኑ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አርሻሎ አርካሌ እየቀረበ ይገኛል።

ጉባኤው ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታው የዞኑ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶችና የፍርድ ቤቱን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 ጠቋሚ ዕቅድ የሚገመግም እና ሌሎች የተለያዩ አጀንዳዎችና የዞኑን የ2018 ረቂቅ በጀትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን