ለሰብአዊ አገልግሎት ሥራ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ አስታወቀ።
የሰው ልጆችን ችግር በማቃለል ተግባር ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተሠማራበት ሁሉ በሀገሪቱ የተለያዩ ሰብአዊ ተግባራትን በመፈጸም ላይ መሆኑ ተመላክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ማህበር በሰብአዊ አገልግሎት ተደራሽነት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት በአርባ ምንጭ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የጋሞ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ስለሺ ሲሳይ የማህበሩ ዓላማ ሰብአዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ በችግር ውስጥ ላሉ የሰው ልጆች አጋርነታችንን ማሳየት በመሆኑ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
ቅርንጫ ጽ/ቤቱ በተለያዩ አከባቢዎች የሚከሰቱ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ችግሮችን ለመቃለል የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የሥራ መሪዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
ዘጋቢ: ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮላንጎ ከተማ እያካሄደ ነው