ከ74 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማግት መቻሉ ተገለጸ
ሀዋሳ: ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ከ74 ሚሊዮን 580 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን ገለፁ።
የደቡብ ትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሔደ ነው።
በ2016/17 ምርት ዘመን የበልግ እርሻ ወቅት በአዝርዕት፣ በፍራፍሬ እና በሆልቲካልቸር ሰብሎች 829 ሺህ 672 ሄ/ር ማሳ በማልማት 74 ሚሊዮን 580 ሺህ 488 ኩንታል ምርት መገኘቱን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።
ኩታ ገጠም እርሻ የክላስተር እርሻ አንዱ የቴክኖሎጂ መሸጋገሪያ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በዓመታዊ ሰብሎች በ745 ቀበሌዎች በ4 ሺህ 145 ክላስተር 155 ሺህ 281 ሄ/ር ማሳ በማልማት 5 ሚሊዮን 726 ሺህ 263 ኩ/ል ምርት መሰብሰቡን አስረድተዋል።
በበጋ መስኖ ልማት በሥራ ሥር፣ በአትክልትና በፍራፍሬ 142 ሺህ 023 ሄ/ር ማሳ ለማልማት ታቅዶ 143 ሺህ 563 እንዲታረስ በማድረግ 142 ሺህ 563 ሄ/ር ማሳ በዘር መሸፈን መቻሉን ጠቁመዋል።
በ2017/18 ምርት ዘመን የበልግ ወቅት እርሻ በአዝርዕትና ሆርቲካልቸር ሰብሎች 777 ሺህ 627 ሄ/ር ለማልማት ታቅዶ 840 ሺህ 584 ሄክታር ማሳ በዘር መሸፈኑም ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በክልሉ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በራስ አቅም ለማቋቋም በተከናወኑ በርካታ ተግባራት ውጤት መመዝገቡ ገልጸዋል።
ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች በአከባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም ብክለትን አስመልክቶ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በ12 ዞኖች መከናወኑን ገልፀው፥ የክልሉ ደን ሽፋን ለማሳደግ 208 ሚሊዮን 487 ሺህ 738 ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል 23.17% የነበረውን የደን ሽፋን ወደ 23.87% ማሳደግ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድዋል።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ
“በክልሉ ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች ለኢኮኖሚ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ ሆነዋል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ