የአስፈጻሚ አካላት ካለባቸው ኃላፊነት መነሻ ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአስፈጻሚ አካላት ካለባቸው ኃላፊነት መነሻ ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል በተለይ ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አሳሰበ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላት የግምገማ መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፥ ምክር ቤቶች በዴሞክራሲ ስርዓት የህዝብ ተሳትፎ የሚገለፅባቸው ተቋማት መሆናቸውን ጠቁመው፥ ካላቸው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ የአስፈጻሚ አካላትን የስራ አፈጻጸም የሚገመገም መሆኑን አስረድተዋል።
እንደክልሉ ምክር ቤት ገለጻ፥ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት በበጀት ዓመቱ ያላቸውን አፈጻጸም ለመገምገም ሲገናኙ ለሁለተኛ ዙር መሆኑን ያነሱት አቶ ወንድሙ፥ አስፈፃሚ አካላት ለህብረተሰቡ አገልገሎት ሊሠሯቸው ካቀዱት ዕቅድ አንጻር ይገመገማሉ ብለዋል።
አስፈጻሚ አካላት ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል ሲባል በተለይ ተግተዉ ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ ወንድሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፥ የክልሉን የአስፈጻሚ አካላት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በየዘርፉ መገምገማቸው የተመላከተ ሲሆን፥ የክልሉን አፈጻጸም በጠንካራና ደካማ ጎን የተለዩ ችግሮችን በቀጣይ ለማረም በሚስችል አኳኋን አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ወግደረስ አማረ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ