የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረጉ
በዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ባሉት የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተደርጓል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደጌላ ኤርገኖ የቦንጋ ዩኒቨርሲት በተለያዩ ዘርፎች ሰራቸው ስራዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን በማንሳት ውጤቱን ለማስቀጠል በየደረጃው ካሉ አካላት ድጋፎች ያስፈልጉታል ብለዋል።
እየተሰሩ ያሉትን ጠንካራ አፈጻጸሞችን አጎልብቶ ማስቀጠል እና ክፍተቶችን ፈትሾ በማስተካከል ዩኒቨርሲቲው እንደሀገር የተቀመጠውን ተልዕኮ መወጣት እንዲችል በጋራ መስራት ይገባልም ብለዋል ፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች የአዳሪ ት/ቤት የግንባታ መዘግየትና ሌሎች አስተዳዳራዊና ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተዋል።
በቀረቡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና አመራር ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብራህ የሚስትሩ ልዩ አማካሪ፣ ፕሮፈሰር ክንዲያ ገ/ህይወትና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በዕውቀት በክሎት የዳበረ ማህበረሰብ በመፍጠር ችግር ፈች ሥራዎችን መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የመምህራን ችግር ለመፍታት በተለያዩ ደረጃዎች በመከፋፈል በተቋም ደረጃ ፣በትምህርት ሚኒስቴር እና በመንግስት ደረጃ በጥናትና በተደራጀ መረጃ ላይ በመመሰረት ምላሽ ይሰጣል ብለዋል የስራ ሃላፊዎቹ።
ዩኒቨርስቲው የዕውቀት መፍለቂያ ቦታ ከመሆኑ አንጻር በጥናትና በዕውነት ላይ በመመስረት ትርጉም ያለውን ውይይት በማካሄድ ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም ሥራ መሰራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት እየተገነባ ያለው አዳሪ ት/ቤት ዓላማው ከሀገርቱ ውስጥ የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ገብተው እንዲማሩ በማድረግ በመልካም ሥነምግባር ታንጸው ሀገራቸውን የሚወዱና ተወዳዳሪና ብቃት ያላቸው ዜጎችን ለማፍራት ታልሞ ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ግንባታው ተጠናቆ መስከረም ላይ ትምህርት ይጀመራል ብለዋል።
ዘጋቢ ፡ መለሰ ገብሬ -ቦንጋ ጣቢያ

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ