የግብርና ሴክተር ምሶሶዎችን በማሳካት የበለፀገ ቤተሰብ ለማየት እተጋለሁ በሚል መሪህ ቃል በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቡታጅራ ከተማ የስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
በክልሉ ከ 7ሺህ 200 በላይ የግብርና ባለሙያዎች የግብርና ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ላይ ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው።
በክልሉ በግብርናው መስክ እየተመዘገበ ለሚገኘው ውጤት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት በመሰኩ ተሰማርተው የሚገኙት የልማት ጣቢያ ሰራተኞች መሆናቸው ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የግብርና እና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፍ አቶ ኡስማን ሱሩር የገለፁት።
በክልሉ የግብርና ሽግግር ለማድረግ ክልላዊ እና ሀገራዊ ተግባር ተቀብሎ ወደ መሬት ለመውረድ በርካታ የግብርና ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ነው አቶ ኡስማን ሱሩር የተናገሩት።
ግብርናውን ይበልጥ ለማዘመንና ውጤታማ ለማድረግ በየአከባቢዎች ያሉንን ሀብቶችን መለየት እና ፈጥኖ ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ መሆኑን ነው የቢሮ ኃላፊው የገለጹት።
በክልሉ እና ከሀገር የተሰጣቸውን የግብርና ተግባራትን ተቀብሎ እስከታች መዋቅር በማውረድ በመስኩ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ነው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ የገለጹት።
በፍራፍሬ እና በሌማት ትሩፋት በዞኑ የሚታይ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ገለጸው ለውጤቱም በመስኩ የተሰማሩ የግብርና ልማት ሰራተኞችን አመሰግናለሁ ሲሉ ነው አቶ ደሱ አበጋዝ የተነገሩት።
ዘጋቢ፡ አብዱልሃፊዝ መሃመድ

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ