በአካባቢው ዘላቂነት ያለው ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ የሸኮና አካባቢው ምሁራን ጥናትና ምርምር ማህበር እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ተናገሩ
የሸኮ እና አከባቢዉ ምሁራን ጥናትና ምርምር ማህበር የ2017 ዓ/ም በጀት አመት ማጠቃለያ ጉባኤዉን በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ አካሂዷል።
በጉባኤው ላይ የተሳተፉ የማህበሩ አባላቶችና ደጋፊዎች በሰጡት ሀሳብና አስተያየት በአካባቢው ዘላቂነት ያለው ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ የሸኮና አካባቢው ምሁራን ጥናትና ምርምር ማህበር እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የምሁራን ማህበሩ ባለፉት ጥቂት አመታት ብሔረሰቡ ዘንድ የሚታዩ የልማት ችግሮች በቅርበት እንዲፈቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በቅርበት በመስራት የላቀ ሚና መጫወቱንም አንስተዋል
በቀጣይም የሸኮ ብሄረሰብ ባህል ታሪክ ወግ እንዲሁም የቋንቋ ልማት ላይ ከሌሎችን ወንድም ህዝቦች ጋር ያለውን አብሮነትና አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር የምሁራን ማህበሩ የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የማህበሩ የበላይ ጠባቂና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ በጉባኤው ማጠቃለያ ንግግራቸው የማህበሩ አባላቶችና ምሁራን በአካባቢው ዘላቂነት ያለው ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ አበክረው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ማህበሩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አመታት የብሔሩን አንድነት ከማጠናከር ጀምሮ በአካባቢው ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ እንዲሁም በህዝቦች መካከል ያለው አብሮነት እንዲጠናከር የሰራቸው ስራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።
በዕለቱ የሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ መምህርና የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሆኑት መምህር ኢህአዴግ ገዳ ማህበሩ በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸውን ስራዎች በጥንካሬና በድክመት ያጋጠሙ ችግሮች ዝርዝር ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በጉባኤው ላይ ከፌደራል ከክልል ከዞንና ከወረዳ የተውጣጡ የተለያዩ አመራሮች እና የሀገርሽማግሌዎችና የምሁራን ማህበሩ አባላቶች ተሳታፊዎች ሆነዋል።
ዘጋቢ :ጦያር ይማም -ከሚዛን ቅርንጫፍ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-