በ2017 የበልግ ምርት ዘመን በግብርና ምክረ ሐሳብና የተሟላ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ስላረሱ የተሻለ ምርት እንደሚያገኙ በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ አንዳንድ አርሶ አደሮች ተናገሩ
በምርት ዘመኑ ለክላስተር እርሻና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ እንደነበር የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።
እየናረ የመጣውን የገበያ ሁኔታ ለመቋቋም ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ባህላቸው ከጊዜ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የሚናገሩት የደቡብ ኣሪ ወረዳ አርሶ አደሮች፤ በመልማት ላይ ባለው የበልግ ምርት ዘመን የግብርና ምክረ ሐሳብንና የተሟላ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ስላረሱ የተሻለ ምርት እንጠብቃለን ብለዋል።
የደቡብ ኣሪ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ደይዳቅ፤ በ2017 በልግ ምርት ዘመን በወረዳው 24 ሺህ ሔክታር መሬት በተለያዩ ምርቶች መሸፈኑን አመላክተው በምርት ዘመኑ ለኩታ ገጠም እርሻ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ እንደነበር አስረድተዋል።
በምርት ዘመኑ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ እንደነበር የሚናገሩት ኃላፊው፤ ከወትሮው ተመሣሣይ የምርት ዘመን የተሻለ ምርት እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።
በቀጣይ አርሶ አደሩ በጊዜ የሚደርሱ ምርቶችን በወቅቱ በመሰብሰብና ለመኸር እርሻ ቅድመ ዝግጅት ላይ እንዲያተኩር መልዕክት ተላልፏል።
ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ