በ2017 የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ
በክልሉ ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትልና የትምህርት ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንደገለፁ፤ በ2017 የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት መፈተኛ ዩኒቨርስቲ እየገቡ ይገኛሉ።
በዚህ አመት በክልሉ ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ የጠቆሙት አቶ አስከብር ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የበይነመረብ ተፈታኝ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ተማሪዎች ተገቢው ክህሎትና እውቀት ጨብጠው በሃገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የመምህራን አቅም የማጎልበት፣ የትምህርት አመራር ሪፎርም የመስጠትና ሌሎችም ተዛማጅ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ነው ያሉት።
በተለይም ካለፉት አመታት በሃገር አቀፍ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶችን በመለየት በክልሉ በሚገኙ ኮሌጆች በመተባበር መምህራን የተለያዩ ጥያቂዎች በመስራትና የማጠናከርያ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎችን የማብቃት ስራ መሰራቱንም አስንስተዋል።
አቶ አስከብር አክለውም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የማረፊያ ዶርምና የምግብ አገልግሎት እንዲያገኙ ዩኒቨርስቲዎች ዝግጁ መሆናቸውን አስገንዘበው፤ ተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት በማድረግ ያለምንም ድንጋጤ ተረጋግተው የተዘጋጀውን ምዘና መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደ ማርያም በበኩላቸው፤ እንደ ጉራጌ ዞን በ2017 በመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ከ1 ሺህ 4 መቶ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስድ ጠቁመው ከ4 መቶ በላይ የሚሆኑት የበይነመረብ ተፈታኞች ናቸው ብለዋል።
በዚህም ተማሪዎች በቴክኖሎጂና በስነ ልቦና ለማብቃት ካለፉት ስድስት ወራት ጀምሮ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።
በዞኑ የሚገኙ በሁሉም አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ተመደቡበት ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በሰላም መግባታቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም ተማሪዎች የፈተናውን ህግና ደንብ በመጠበቅ ከኩረጃ ነፃ በሆነና በተረጋጋ መንፈስ መፈተን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-