ባለፉት 11 ወራት ብቻ በቤንች ሸኮ ዞን በትራፊክ አደጋ የ32 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
በቤንች ሸኮ ዞን በትራፊክ አደጋ የሚደርሰው ጉዳት በየጊዜው እየተባባሰ መምጣቱን የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ገለፀ።
ባለፉት 11 ወራት ብቻ በዞኑ በደረሱት 129 አደጋዎች የ32 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልፇል ።
በመምሪያው የትራፊክ ደህንነት መረጋገጫ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ተደሠ ከተማራሻ እንደገለጹት በዞኑ የትራፍክ አደጋ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ ነው፡፡
ባለፉት 11 ወራት ብቻ በዞኑ በደረሱት 129 አደጋዎች የ32 ሰዎች ሕይወት ስያልፍ 77 ከባድና 18 ቀላል እንዲሁም በአደጋው ከ5ሚለዬን በላይ ንብርት መወደሙን ገልጸዋል፡፡
አደጋው ከተመሳሳይ ወቅት ጋር ስነጻጸር 30 በመቶ መጨመሩን የገለጹት አቶ ታደሠ በዚህም ህይወታቸውን የሚያጡና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥር እንዲሁ ጭማሬ ማሳየቱም ተናግረዋል፡፡
በተለይ የመንገድ ብልሽት፤ የአሽከርካሪዎች ቼልተኛነት፤ ከአቅም በላይ መጫንና የተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ችግረ ለአደጋው ዋና ዋና መንሰኤዎች መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዞኑ አደጋውን ለመቀነስ ለትራንስፖረት አመቺ ያልሆኑ መንገዶች እንዲጠገኑ የማድረግ፤ የቁጥጥርና ክትትል ስራዓቱን ማጠናከርና ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ስራዎች መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም የፍጥነት ወሰን ለመገድብ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በሚደረገው ርብርብ ከአሽከርካሪዎች በተጨማሪ እግረኞች የትራፊክ ህጎችን ማክበር እንዳለባቸውም ነው አቶ ተደሠ መልዕክት ያስተላለፉት፡፡
ዘጋቢ፡ በየነ ወርቁ-ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ