የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር የቱሪስት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ላይ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል::
ክልሉ በሆቴል ኢንቨስትመንት ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኑሪ ከድር ዘርፉን የሚቀላቀሉ አዳዲስ ሆቴሎች በመኖራቸው ብቃታቸውን ማረጋገጥ አስፈልጓል ነው ያሉት።
ይህ መድረክ የብቃት ማረጋገጡን ስራ ከንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር በቅንጅት መስራትን ያለመ መሆኑ ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል።
ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጡና በኮከብ ደረጃ የሚመደቡ ሆቴሎች እንዲበዙ ለሚሰሩ ስራዎች ቢሮው ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ተብሏል።
የሆቴል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ብቃት እንዲረጋገጥ የሚያስችል ስራ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሲሰራ የንግድ ስርዓቱ ህጋዊ እንዲሆን ያስችላል ያሉት የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ምክትል ቢሮ ሃላፊ ቀመሪያ ረሻድ ይሄም የሁለቱን ቢሮዎች ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነት ያሳያል ብለዋል ::
በመድረኩ በሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ዘርፍ
የነበሩ ጉድለቶችን በማረም የሆቴል ኢንቨስትመት ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
ዘጋቢ:ሲሳይ ደበበ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-