የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሂደት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሂደት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የአርባምንጭ ከተማ አሰተዳደር ፍትህ ጽህፈት ቤት ገለፀ።
በህብረተሰቡ ዘንድ በየጊዜው የሚከሰቱ ከልደት እስከ ሞት ያሉ ኩነቶችን በወቅቱ የማስመዝገብ ግንዛቤ ማደጉም ታውቋል።
የወሳኝ ኩነት መረጃ ለመልካም አስተዳደርና ለሀገራዊ ልማት እድገት ከፍተኛ ግብአት መሆኑ ይታወቃል።
የአርባምንጭ ከተማ አሰተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ብዙነህ እንዳስረዱት ወሳኝ ኩነት ከውልደት እስከ ሞት የሚከሰት የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ እና ማህበራዊ ህይወትን የሚዳስስ መሆኑን ተናግረዋል።
የኩነቶች ምዝገባ በወቅቱ ማከናወን ከሀገራዊ ጠቀሜታ ረገድ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ሂደቱን ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባር ሲሰራ መቆየቱን ኃላፊው ገልፀው፥ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና ሞት ወቅታዊ ኩነቶች እንደተከሰቱ በወቅቱ ከማስመዝገብ አኳያ በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚስተዋለው የግንዛቤ ችግር እያደገ በመምጣቱ የምዝገባ ሽፋኑ እድገት ማሳየቱን ኃላፊው አክለዋል።
የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የአግልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ነው አቶ ተሰፋዬ ያስረዱት።
የአርባምንጭ ከተማ አሰተዳደር ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዳይሬክቶሬት አሰተባባሪ አቶ ደመላሽ ካንኮ በበኩላቸው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ልምድን ህብረተሰቡ እንዲያዳብር ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በተለይ በጤና ተቋማት የልደትና ሞት ኩነት ሠርተፍኬት ያለምንም ክፍያ እንደሚሰጥ ጠቁመው ህብረተሰቡ ወቅታዊ ምዝገባን በማከናወን ከአላስፈላጊ እንግልትና ውጪ ራሳቸውን እንዲታደጉ አሳስበዋል።
አቶ ሽመክት መድህን በአርባምንጭ ከተማ ወሳኝ ኩነት መዝገብ ሹም ዘንድ በመቅረብ ከትዳር አቻው ጋር ጋብቻ በመፈጸም ባገኙት የጋብቻ ሰርተፍኬት እና ፈጣን አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ አለሚቱ አረጋ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ፅዳትን ባህል ማድረግ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ነፍሰጡር እናቶች ድጋፍ ተደረገ
ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ኮረሪማን በማምረት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማደረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ