የአካባቢ ብክለትን በዘላቂነት በመከላከል የተሻለች ሀገር ለትውልድ ለማውረስ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
“ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛ ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መድረክ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ ተካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የጋራ ምክክር፣ የከተማ ፅዳትና የችግኝ ተከላም ተከናውኗል።
በንቅናቄው መድረክ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፤ ህብረተሰቡን በማስተባበር የሚሠሩ ሥራዎችን በማጠናከር የተሻለች ሀገርን ለትውልድ ለማውረስ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንደገለፁት፤ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማንቃት ብክለትን ለመከላከል የቆሻሻ አያያዝ ሥርዓትና የአካባቢ እንክብካቤ ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።
የአሪ ዞን ደንና አካባቢ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሣሁን ጠቃይ በበኩላቸው፤ ለ6 ወር በሚቆይ ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መድረክ “ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ” በሚል መሪ ቃል የፕላስቲክ፣ የአፈር፣ የውሃና የድምፅ ብክለትን በመከላከል በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ የወጡ ሕጎችን ለማስፈፀም እንደሚተጉ ተናግረዋል።
ዘላቂ የከተማ ፅዳትና ውበት ሥራዎችን በማጠናከር ብክለቶችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በትኩረት ይሠራል ያሉት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ