በወረዳው በተሠሩ ሥራዎችና በቀጣይ ተግባራት ላይ የሴቶች ሚናን ትኩረት ያደረገ ውይይት ከወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሴት የመንግስት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደርጓል።
የይርጋጨፌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ሴቶች እንደ ሀገር በሚሠሩ ሥራዎች በሁሉም ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎች አሉ የሚሉት አስተዳዳሪው፤ ይህን ምቹ ነባራዊ ሁኔታ መጠቀም አለባቸው ብለዋል።
ሴቶችን ለመደገፍ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆናቸውን ያመላከቱት አቶ ዳዊት ቡኔ፣ ዘመኑ የውድድር በመሆኑ በሁሉም ዘርፎች ተወዳዳሪ መሆን እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል።
ሴቶች በየተቋማቸው ያለውን መልካም ጅማሮዎችን ማስቀጠልና ደካማ ጎኖችን ለማረም መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የምስራች ከፍያለው፤ መድረኩ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በሚሠሩ የልማት ሥራዎች የሴቶችን ሚና የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ መስተዋት ጥላሁን፣ ዘማነሽ ኤዴማ እና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት፤ በወረዳው እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸውና በተለያዩ ዘርፎች ጠንካራ ሴቶች በመኖራቸው ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የዕጩ ማስተዋወቂያ እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አካሄደ
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የአይን ህክምና በሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ብልጽግና ፓርቲ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ በውጤታማነት ለአገልግሎት እያበቃ ነው – ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ